ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና

ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ60 በላይ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ለቤተመንግስት ማስፋፊያ በሚል በመንግስት ሀይሎች መፍረሳቸው ተነገረ
ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ብሎክ አንድ ፤ሶስት እና አራት የሚገኙ ነዋሪዎች ቤታችን በሕግ ወጥ መንገድ በመንግስት ሀይሎች ፈርሶብናል ብለዋል፡፡ የቀጠና አንድ ቁልቢ ኮሚቴ አመራሮች እንደተናገሩት ከሆነ ከ60 እስከ 65 የሚደርሱ ቤቶች በቀን 17 2/2015 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች ከጠዋቱ 11፡30 ጀምሮ በኃይል ፈርሰዋል ፡፡ ቤቶቹ የፈረሱት አዲስ ይገነባል በተባለው የቤተ-መንግስት ፕሮጀክት ውስጥ ገብተው በመገኘታቸው More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ድጋፍ ሰጪ በሰሜን አሜሪካ
በእስክንድር ላይ የተፈጸመው ጥቃት ፤የፍትሕ ሥርዓቱ ዝቅጠት ማሳያ ነው !!!

ህመሙ _አመመኝ
አቶ ስንታየሁ ቸኮል የኅሊና እስረኛ ከቂሊንጦእስክንድር ነጋ የድርጅቴ መሪ ራስ ነው! ለኔ ደግሞ የሥራ አለቃዬ ነው!እስክንድር ታላቅ ወንድሜ መካሪዬ ነው። እስክንድር ለጋራ መስዋዕትነት የተጠራን የቁርጥ ቀን የሀገሬ ሕብረ_ቀለም ሃቀኛ ጓዴ ነው።ከመሪዬ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን በተቀራረበ መኝታ ላይ እንዴት እንዳዳረ አውቃለሁ። ህመሙ- አመመኝ… ላብ በሚያጠምቅ ምጥ ..እእእእእ… የጥዝጣዜ ስሜት ቦታው ላይ መፍትሄ አጥተህ መጋራት More/ተጨማሪ…
ጋዜጣዊ መግለጫ

ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!
ባልደራስ ሊያካሂደው የነበረውን የምርጫ ቅስቀሳ ሰረዘ !!ከሁሉ አስቀድመን በአገራችን በኦሮምያ ክፍለ-ሃገር በተለያየ ወቅት በተደጋጋሚ በተፈጸመ ጥቃት ፤ በንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና ኦነግ ሸኔ በተባለ የዳቦ ስም የተሰጠው ገዳይ ቡድን አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ እውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ይገልጻል!የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡በንጹሃን More/ተጨማሪ…
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀልን በጽኑ እናወግዛለን !
ባለፉት ዓመታት በተለይ “ለውጥ” መጣ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በዜጎች ላይ የሚፈፀመውን የዘር ፍጅት ወንጀል በአይነቱ እና በመጠኑ እየጨመረ መጥቷል ። ለዚህም ዋንኛው ምክንያት አሁን በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት እንደሆነ ብዙ አስረጂ የሚሻ ጉዳይ አይደለም ።በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ጋምቤል ወረዳ ቦኔ ቀበሌ የተፈጸመው የዘር ፍጅት ወንጀል ከዚህ ቀደም በክልሉ ሲፈጸም ከነበረው አረመኔያዊ More/ተጨማሪ…
We strongly condemn the genocide
It was learnt that genocidal acts were committed in West Wollega Zone Bone Kebele in March 31, 2021. Balderas for True Democracy strongly condemn the genocide which has been taken as a normal social practice during the Abiy’s Administration. We are deeply saddened by the news and may God give the victims eternal rest.The genocide More/ተጨማሪ…

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ትብብርን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የሀገራችን ህዝብ ለዘመናት በተጫኑበት ኢዲሞክራሲያዊና አምባገነን አገዛዞች የተነሳ፣ በነጻነት እጦት፣በስቃይ እና በመከራ ኑሮውን እንዲገፋ ተደርጓል። ጭቆናን አስወግዶ የሚፈልገውን ፍትህ እና እኩልነት እውን ለማድረግ ከፍትኛ ዋጋ መክፈሉም እሙን ነው።ይሁንና የሃገራችን የለውጥ ፍላጎት እና እንቅስቃሴ ጅማሮው ሳይሳካ፣ ለቀጣዩ ዴሞክራሲያዊ ትግል ተስፋ ሊሆን የሚችል መሰረታዊ የትርክትና የመዋቅር ክለሳ እንኳ ሳይደረግ አምባገነንነትና ዘረኝነት የእጅ ለውጥ ብቻ እያደረጉ የሚፈራረቁባት ሆናለች። More/ተጨማሪ…
መጣጥፍ – ነፃ አስተያየት
የኢትዮ ቴሌኮም ሽያጭ ጥቅምና ጉዳት ጉዳይ ሙያዊ ቅኝት (ነብዩ ውብሸት)
አፄ ምኒሊክና የመጀመሪያው የስልክ ግንኙነት ኢትዮጵያ፣በ1886ዓ.ም፣በታላቁ ንጉሠ ነገሥት አፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት፣ የመጀመሪያውን የ477 ኪ.ሜ የስልክ መሥመር ዘርግታ፣“ጤና ይስጥልኝ ዐዲስ!! ጤና ይስጥልኝ ሐረር!!” ካስባለች፣126 ዓመታት ተቆጠሩ። አፄ ምኒሊክ፣ሀገሪቷን ያስተዳድሩ በነበሩበት ዘመን ያስገቧቸውን፣ዘመናዊ አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን ብዛት ስናይ፣አፄ ምኒሊክ፣“የሥልጣኔ ማግኔት ነበሩ!!” ለማለት እንችላለን። አፄ ኃይለሥላሴና የቴሌኮሙኒኬሽን እድገት ኹኔታ የቴሌፎን ቴክኖሎጂ ወደ ኢትጵያ የገባው፣በ1886 ዓ.ም በምኒልክ More/ተጨማሪ…
ዘር ማጥፋት ወይስ ሰብዓዊ ፍጡር ላይ የተፈጸመ ወንጀል?
እስክንድር ነጋ፣ የህሊና እስረኛ፤ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት፣ አዲስ አበባከሁሉ አስቀድሞ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሀጫሉ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ ክልል ስለተከሰተው ሁኔታ ያወጣው ሪፖርት ምሥጋና ይገባዋል፡፡ የሚንቀሳቀስበትን አውድ ግምት ውስጥ እናስገባለት፡፡ ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ብዙ በጐ እሴቶች ያሏት ሀገር መሆኗ የሚካድ ባይሆንም፣ በሰብዓዊ መብት አክባሪነታቸው ከሚወደሱ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ግን አልታደለችም፡፡ በፍጥነት የሚበቅልና የሚለመልም More/ተጨማሪ…
ውስጠ ወይራው ያለመለወጥ ‹ለውጥ› (፪)
በክፍል አንድ መጣጥፌ ‹ለውጥ› እየተባለ የሚወራው ሀሰት መሆኑን አብራርቻለሁ፡፡ ‹ለውጥ› ተብየው ውስጠ ወይራ እንደሆነ እና ‹የለውጡ› መሪ ነኝ ባዩ አብይ አሕመድ ነብረው የወጡት ወያኔ የጣለውን እንቁላል እንደሆነ አብራርቻለሁ፡፡ በ‹ለውጥ› ሽፋን ‹ለውጥን› የመከላከል ቁልቁለቱ አያሌ ርዕዮተ ዓለማዊ፣ ሕገ መንግሥታዊ፣ ተቋማዊ እና ሥርዓታዊ መገለጫዎች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ሦስት መገለጫዎችን ቀንጭቤ እገልፃለሁ፡፡ አንደኛው የአዳፍኔነትና የአስቀጣይነት መንታ ስለት ሲሆን More/ተጨማሪ…
“ገበታ ለሀገር” – ከዶሮና ዓሳ ወግ አንጻር(ከማለፊያ ደርሰህ)
ዶሮና ዓሳ የቀረበ ገበታ አይተው ወግ ይጀምራሉ:: በገበታው ላይ የቀረበው ምግብ የዕንቁላል ጥብስና ዓሳ ነው:: ዶሮው “ይህ ገበታ ጣፋጭ ሆኖ ትላልቅ መሳፍንትና መኳንንት ተደስተው እንዲመገቡ ለማድረግ የእኔ አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ነው:: ምክንያቱም እንቁላሉን የጣለችው ሚስቴ ዶሮ ነች፤ እንቁላሉ የሁለታችንም ዶሮዎች አበርክቶ ነው” ብሎ ተኩራራ::ዓሳውም ተደንቆ “እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳሉ” ብሎ ተረተና “ሰማህ ዶሮ፣ More/ተጨማሪ…