“ፍትሕ ለግፍ እስረኞች ” የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ!

የሞራል ግዴታችንን እንወጣ !
ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ላሉት ለሀገርና ሕዝብ ተቆርቋሪ፣ የሰላም ታጋዮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ አስካለ ደምሌ ጎን መቆማችንን በተግባር እናሳይ። ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 9, 2014 ዓ. ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንገናኝ።

ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧት 3 ሰዓት ላይ ችሎት ይቀርባሉ።በመሆኑም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ላይ በመገኘት ክርክሩን እንድትዘግቡ ባልደራስ ጥሪ ያቀርባል።

የነገ ቀጠሮ ጥቅምት 9 / 2014 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት
ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ላሉት ለሀገርና ሕዝብ ተቆርቋሪ፣ የሰላም ታጋዮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም፣ አስካለ ደምሌ ጎን መቆማችንን በተግባር እናሳይ። የሞራል ግዴታችንን እንወጣ! ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 9, 2014 ዓ. ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንገናኝ።
ዳኛው የሉም? (ጌጥዬ ያለው)
በእነ እክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ከዚህ በፊት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና ሰበር ሰሚ ችሎት “ዳኞች ተሟልተው አልቀረቡም”፣ “መዝገቡን አልመረመርንም”፣ “ፕላዝማ ተበላሽቷል” በሚሉ ሰበቦት እስከ አንድ ወር ድረስ የረዘሙ ተለዋጭ ቀጠሮዎች ይሰጡ ነበር። በዚህም ምክንያት ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይቅረቡ?፣ ከመጋረጃ ጀርባ ይቅረቡ?፣ በዝግ ችሎት ይቅረቡ በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሲሟገቱ ከአንድ አመት More/ተጨማሪ…
ችሎት፤ ጥቅምት 5 ቀን 2014
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። ዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን በግለፅ ችሎት እንዲያሰማም ለዛሬ ከቀትር በኋላ ማለትም ከቀኑ ከ7:30 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። More/ተጨማሪ…
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “የፈራ ይመለስ” መፅሐፉ ላይ እስክንድር ነጋን እንዲህ ሲል ገልፆታል።
“እስክንድር ነጋ ለእኔ ከነ አሉላ አባ ነጋ፣ከእነ ዘረዓይ ደረስ፣ ከነ አብዲሳ አጋ ትይዩ የሚቆም የአገር ባለውለታ ጀግና ነው። “
”የያዝኩትን መሬት ኢትዮጵያዬን እንዳልለቅ የመንፈስ ብርታት የሆነኝም ይህ ሰው ነው።”
https://www.facebook.com/Balderas.Ethio/photos/a.103738714595344/482835816685630/?type=3&eid=ARBksvkYg7qcg-863YCkyn_7FnaZ0rBcGghJjzcpr2uImiUa57luD-2tCqJsKKpivvaOG25g-wVaHEK8&__xts__%5B0%5D=68.ARB_cVCj-XaYkJfJGj0WrRut8BSz_rxVbyXwBvEYDXhxCQx_g3rELsGNdwrRys8hzzu5ZcOoio2HFauPGWNUYMzCMIEdX2UhACEEZYjXazz7cZTxT_JPXsZHwtIwBUDkYKSte2i7gBuWlHNH_mUTuJyibq1kz-_b0L_rSZFa2-ZuhgOGLBE07aN11faIWYds5IbHpoIpkYk_-yD-hMRiodFwaWThzGGqeITqKftf4OEMMCTCjINafMtEez9H-JSHjtCHYy4CLoP-K91gglfsil_OKcnufUeJByFsYGffJ0kMYqlWm-U&__tn__=EHH-R
ዜና

ነገም እንደዛሬው የሞራል ግዴታችንን እንወጣ!
በዛሬው የእነ እስክንድር ነጋ ችሎት ላይ ለመታደም የፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ መጥታችሁ ‘አዳራሽ ሞልቷል’ በሚል ችሎቱን ሳትታደሙ የተመለሳችሁ የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ተቆርቋሪዎች በርካቶች ናችሁ። ከኅሊና እስረኞች ጎን መሆናችሁን ስላሳያችሁን በእጅጉ እናመሰግናለን።ችሎቱን የታደማችሁም ሆነ የተከለከላችሁ አጋርነታችሁን አሳይታቸሰኋልና ፈጣሪ አጋር ይሁናችሁ። የሞራል ግዴታችሁን መወጣታችሁ በታሪክ ተመዝግቦ ለትውልድ እንደሚተላለፍም ተስፋ እናደርጋለን።ችሎቱ ነገም ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. More/ተጨማሪ…

ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድ ነጋ ላይ የሚቀርቡ ምስክሮች ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ ያቀረበውን አቤቱታ ፍ/ቤት ውድቅ አድርጎታል
በዚህም መሰረት ፦በነ #እስክንድር ነጋ ላይ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ዐቃቤ ሕግ የዘረዘራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር:-1. ፈንታሁን አሰፋ2. መንበረ በቀለ3. ወርቁ ታደሰ4. ፍፁም ተሰማ5. ደረጀ ግዛው6. ቴዎድሮስ ለማ7. ያየህ ብርሃኑ8.ጌትነት ተስፋዬ9. ትንሳኤ ማሞቀሪ የ12 ምስክሮች ስም ዝርዝር ነገ ጧት እንዲቀርብ ታዝዟል። ከላይ ከተጠቀሱት መካከል ሁለቱ ነገ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ More/ተጨማሪ…

የችሎት ክለሳ
ጌጥዬ ያለውየፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የእነ እስክንድር ነጋን መዝገብ ቁጥር 260175 ገልጦ የይስሙላ ክርክሩ ቀጥሏል። ባለፈው ጥቅምት 5 ቀን በተቀጠረው መሰረት ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት እንዲያቀርባቸው የታቀዱ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን፤ በተለይም ከሳሽ እንደ እንኩሽ በሚፈራው ፌስቡክ ይገለፅ More/ተጨማሪ…
ጋዜጣዊ መግለጫ
የባልደራስ የምርጫ ዘመቻ ዝግጅት ማብቂያ ፕሮግራም ላይ የተደረገ ንግግር
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ባለፉት አራት ወራት የቅድመ ምርጫ እንቅስቃሴው በሃራዊ እና በአዲስ አበባ ነክ ጉዳዮች ፓርቲው የሚያራምደውን ፖሊሲዎች ለከተማው ሕዝብ በተለያዩ መድረኮች እና የቅስቀሳ ዜዴዎች ለማሳገንዘብ ጥረት ሲደርግ ቆይቷል፡፡ በሃገር አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለውን አመለካከት በሃገር አቀፍ ማኒፌስቶው አስፎሮ አሰራጭቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማን ሕዝብ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም በሚካሄደው ምርጫ ቢመርጠው፣ ስር የሰደዱ የከተማይቱን More/ተጨማሪ…
የሐዘን መግለጫ
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት የሰማነው፣ በጥልቅ የሐዘን ስሜት ነው፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣የኢትዮጵያ፡ቁዋንቁዎችንና ፡ሥነጽሑፍ እንዲኹም ታሪክ አስመልክተው ፣አያሌ የጥናትና የምርምር መጻሕፍትን ያበረከቱ ብርቅ፡ኢትዮጵያዊ፡ምሁር፡ነበሩ።የቋንቋ ፣የሥነ ጽሑፍ፣የታሪክና የሥነመለኮት ሊቁ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ በተለያዩ አገራዊና አህጉራዊ የፖለቲካ እድገት አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ነክ ጉዳዮች ላይ ይሰጡዋቸው፡በነበሩቱ በሳል ሀሳቦቻቸው እና ትችቶቻቸው ይታወቁ፡ነበር።እኚህ ሀገራቸውን ወዳድ፣ ዓለም አቀፋዊ ምሁር More/ተጨማሪ…
መጣጥፍ – ነፃ አስተያየት

If the great Eskindir becomes the mayor, Addis Ababa will get the best leader in her history.
What is your choice if you don’t vote for Balderas? (Yared Tibebu, those who were the fighters of E.D.N) … Eskindir may not have technical knowledge to lead Addis Ababa. However, a qualified municipality manager (professional) can hire. Even with technical knowledge, the mayors of Addis Ababa who were displaced for 30 years cannot compete More/ተጨማሪ…