ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
የግፍ እስረኞቹ አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ነገ እና ከነገ ወዲያ ፍ/ቤት ይቀርባሉ
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ባለፈው ታህሳስ 06/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ችሎቱም ተጨማሪ 7 ቀናትን ሰጥቶባቸው ነበር። በዚህም መሰረት ነገ ሀሙስ 13/04/2015 ዓ.ም በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡ ይሆናል። ሌላው በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ የምክር ቤት አባል እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት More/ተጨማሪ…
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች የምስራቅ ወለጋ አጎራባች በሆነው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ ታህሳስ 01/2015 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የሰባቱን ሟቾች አስከሬን ብቻ መቅበር ተችሏል፡፡ በሀይል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡት የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የተገደሉ ህፃናት፣ሴቶችና አዛውንቶች አስከሬን በየጫካው ወድቆ More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ፓርቲው አቶ ካሳሁን ደስታ በፖሊስ ታገቱ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ንቁ አባል እና ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ዛሬ ጠዋት፤ በትላንትናው ዕለት 03/04/2015 ዓ.ም ለታሰሩት አቶ ናትናኤል ስንቅ ለማቀበል ሄደው ነበር። ሆኖም በሄዱበት ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ (ላዛሪስት ፔኒሲዮን) የሚገኘው የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በዛው አግቶ አስቀርቷቸዋል።አቶ ካሳሁን ፓርቲያቸውን እና ሀገራቸውን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ ሰላማዊ-ታጋይ ናቸው።
ጋዜጣዊ መግለጫ
ለባልደራስ አባላት እና ደጋፊዎች በሙሉ
ቀን፡-03/02/2015 ዓ.ም ቅዳሜ ጥቅምት 5/2015 ከ6:00 እስከ 10፡00 ሰዓት የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴም ሆነ ብሔራዊ ምክር ቤቱ የጠሩት በፓርቲው የጽ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ስብሰባ የሌለ መሆኑን ለፓርቲያችን አባላት በሙሉ እንገልፃለን፡፡ በጽ/ቤታችን የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ስብሰባ አለ ብሎ የጠራው ህገ ወጡ አፍራሽ ቡድን መሆኑ ታውቆ፣ አቶ እስክንድር ያቋቋመውን እና በርካታ አባላት መስዋእትነት የከፈሉበትን ፓርቲ ህልውና ለማስቀጠል More/ተጨማሪ…
የወቅቱን የሃገራችንን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ሁኔታ በማስመልከት ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በእርስ በርስ ጦርነት ፣ በርሃብ፣ የነገድ ፖለቲካ ባስከተላቸው ቀውሶች፣ በፍትህ እጦት፣ በኑሮ ውድነት፣ ወዘተ… እና በሌሎችም አሳዛኝና አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገጠሟት እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ወቅቶች መሃከል ይህ አሁን ያለንበት እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምዕራባውያን ሀገራት ከረጅም ጊዜያት አንስቶ ኢትዮጵያን በእነሱ ተጽዕኖ ሥር ለማድረግ ‹‹አማራን ማዳከም ይገባል›› More/ተጨማሪ…
” የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም። ድምፅ ተዘርፏል”
የስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለይ የአዲስ አባባ የቅድመ ምርጫ ሂደት እና የድህረ ምርጫ የነጻ፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ መሆኑን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል። “ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ዘርፈውታል። ይህም በመሆኑ በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለው” ብሏል ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የምርመራ ውጤት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ More/ተጨማሪ…
በምርጫው ጉዳይ ላይ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛ አገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ በማሰባሰብ አጠናክሮ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ፣ በድምጽ አሰጣጡ እና ቆጠራው የነበሩ ችግሮችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ፓርቲያችን አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ More/ተጨማሪ…
መጣጥፍ – ነፃ አስተያየት
ጦርነት የግድ ከሆነ !
የሀሰት ክስ እየተመሰረተብኝ በእስር ያሳለፍኳቸው ዓመታት ይኸው ዘንድሮ አሥራ አንድን ረግጠው አልፈዋል፡፡ በወራት መቁጠር ካቆምኹኝ እንደሆነ ቆይቻለሁ፡፡ እሥረኛውን ዓመት አሰልቼ መቶ ሃያ ሲሆንብኝ፣ ለእኔም ለአድማጩም ስለ ወራት ማውራቱ ይሻላል ብዬ ወሰንኹ፡፡ ያለቅጥ ከብዶ እንዲታይ አልፈልግም፡፡ ለዚህች ሀገር ዲሞክራሲ ከእኔ በላይ የከፍሉትን ሳስብ አንገቴን እደፋለሁ፡፡ አካላቸው የጎደለ፣ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉት ደግሞ አንደበቴን ይቆልፉታል፡፡ የአሥራ አንዱን ዓመታት More/ተጨማሪ…
If there must be war in Ethiopia…
A prisoner of conscience for many of the past 15 years, Eskinder Nega smuggled out the following plea from his detention in Addis Ababa.If not in how my incarcerators have treated me, then in how I have been handed by government sponsored trolls on the internet, this episode of my eleven years (and counting) imprisonment More/ተጨማሪ…
ዋልጌ ዳኞች! ጌጥዬ ያለው
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድር ነጋ (5 ሰዎች) ላይ በከፈተው ዶሴ ያሉትን የሰው ምስክሮች እንዲያሰማ አዝዟል። በመሆኑም ሀምሌ 8፣ 9፣ 14፣ 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም. 21 ምስክሮችን በግልፅ ችሎት እንዲያቀርብ ተወስኗል። በዚሁ መሰረት ቢጠበቅም ዐቃቤ More/ተጨማሪ…