ዜና(News)
አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ በአገዛዙ ሀይሎች ታፈነ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው አቶ ናትኤል ያለምዘውድ ዛሬ ታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ከመኖሪያ ቤቱ በአገዛዙ ሀይሎች ታፍኖ መወሰዱን ቤተሰቦቹ ተናግረዋል፡፡ የግፍ እስረኛው ናትኤል ያለምዘውድ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ እስር ላይ ይገኛል። የግፍ እስረኞች ይፈቱ! ድል ለዲሞክራሲ!
ሁለቱም የግፍ እስረኞች ለ ታህሳስ 19 ተቀጠሩ
የባልደራስ ፓርቲ አባል የሆኑት የግፍ እስረኞች አቶ ካሱ ደስታና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበዋል። በዚህም መሰረት:- በትናንትናው ዕለት (13/04/2015ዓ.ም) አቶ ካሳሁን ደስታ በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መቅረባቸው ይታወሳል። ችሎቱም የፖሊስን መዝገብ ለመመርመር ለአዳር ቀጥሮ ነበር። ፖሊስ ባቀረበው መዝገብ የሶስት ሰዎች ቃል የተቀበለ መሆኑን ገልጿል።ችሎቱ በትላንትናው እለት ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀናት More/ተጨማሪ…
የግፍ እስረኛው አቶ ካሳሁን ለይደር ተቀጠሩ
በሀሰት ክስ ለታሰሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ስንቅ ለማቀበል እና ለመጠየቅ በሄዱበት በፖሊስ ታግተው እዛው የቀሩት አቶ ካሳሁን ደስታ ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ በቀጠሯቸው መሰረት ፍ/ቤት ቀርበዋል።ፓሊስ በዛሬው ችሎት ላይ አቶ ካሳሁን ሌላውን እስረኛ አቶ ናትናኤልን ለመጠየቅ በሄዱበት እንዳሰራቸው ክዷል። ይባስ ብሎም አቶ ካሳሁንን ያሰረበትን ምክንያት ሲናገር ”በአምሀ ደስታ ት/ቤት በነበረው ተቃውሞ ላይ ከኋላ መኪና ይዘው ሲያስረብሹ More/ተጨማሪ…
የግፍ እስረኞቹ አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ነገ እና ከነገ ወዲያ ፍ/ቤት ይቀርባሉ
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ባለፈው ታህሳስ 06/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ችሎቱም ተጨማሪ 7 ቀናትን ሰጥቶባቸው ነበር። በዚህም መሰረት ነገ ሀሙስ 13/04/2015 ዓ.ም በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡ ይሆናል። ሌላው በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ የምክር ቤት አባል እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት More/ተጨማሪ…