ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
ህመሙ _አመመኝ
አቶ ስንታየሁ ቸኮል የኅሊና እስረኛ ከቂሊንጦእስክንድር ነጋ የድርጅቴ መሪ ራስ ነው! ለኔ ደግሞ የሥራ አለቃዬ ነው!እስክንድር ታላቅ ወንድሜ መካሪዬ ነው። እስክንድር ለጋራ መስዋዕትነት የተጠራን የቁርጥ ቀን የሀገሬ ሕብረ_ቀለም ሃቀኛ ጓዴ ነው።ከመሪዬ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ ሆነን በተቀራረበ መኝታ ላይ እንዴት እንዳዳረ አውቃለሁ። ህመሙ- አመመኝ… ላብ በሚያጠምቅ ምጥ ..እእእእእ… የጥዝጣዜ ስሜት ቦታው ላይ መፍትሄ አጥተህ መጋራት More/ተጨማሪ…
የእስክንድር እግር መሰበሩ በህክምና ተረጋገጠ !
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዕቅድ የተደበደበው እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ሆስፒታል በተደረገለት ህክምና ፣ በግራ እግሩ ላይ ያለው አውራ ጣቱ መሰበሩ በራጂ ተረጋግጧል።በዚህም መሠረት፣ ለሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታት የሚቆይ ጄሶ ተደርጎለታል።እስክንድር ከማረሚያ ቤት ሆኖ ባስተላለፈው መልዕክት፣ “በሰሜን ያለውን ጦርነት አስባለሁ። የታሰሩትን አባሎቻችንን አስባለሁ። አጥንታችንን መስበር ይቻላል። ትግላችንን ግን መስበር አይቻልም More/ተጨማሪ…
በጅምላ ከታሰሩት መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጠሩ !
የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 ዓ/ም የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ ታፍሰው መታሰራቸው ይታወቃል።አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት የሰሙ ታዳሚዎች እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው የወጡ ሲሆን ፤ ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ More/ተጨማሪ…
ጋዜጣዊ መግለጫ
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የምርጫ ቦርድ አሻጥር አስመልክቶ ከባልደራስ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !
1ኛ. ከሁሉ አስቀድመን፣ በአገራችን ምዕራብ ኦሮምያ ክልል፣ ወለጋ ውስጥ፣ በሆሮጉድሩ ወረዳ ውስጥ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ከ60 በላይ ንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ ይገልጻል፤ የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ፓርቲያችን በአማራ እና More/ተጨማሪ…
መንግሥት በአማራ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ እንዲቆም እንጠይቃለን!
በኦሮሚያ፤ ሆሮጉድሩ ወለጋ አቤ ደንጎሮ አማራዎች ካለፈው ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ በነሲብ እየተገደሉ ነው። የሚገደሉትም በመንግሥታዊ የእዝ መዋቅር በታገዘ ታጣቂ ቡድን ነው። ከግድያ የተረፉት ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ሕፃናት እየታነቁ ወንዝ ውስጥ መወርወራቸውንም ከአካባቢው የወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። በጉጂ፤ አማሮ ተመሳሳይ ብሔር ተኮር ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው።በመሆኑም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) More/ተጨማሪ…
ለእውነተኛ ፍትህ የሚጨነቅን ሰው በፍትህ ዕጦት ማስጨነቅ የግፍ መጨረሻ ነው !!
የባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ባልተገኙበት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ተገቢነት የለውም።አቃቤ ሕግ ምስክሮችን በግልፅ ችሎት አቅርቤ ምስክር ማሰማት አልችል በማለት ሰበብ መሪዎቻችን የተፋጠነ ፍትህ እንዳያገኙ እየሰራ መሆኑን ከጅምሩ ፓርቲያችን ይረዳል።ጠ/ፍ/ቤቱ የቀጠሮ ቀን ከመወሰኑ አስቀድሞ የመከራከሪያ ጭብጡን ግልባጭ ጠበቆቻችን በተደጋጋሚ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምላሽ ሳያገኙ More/ተጨማሪ…
እንኳን ለ43ኛው የካራማራ የድል በዓል አደረሠን!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ለካራማራ ጀግኖች መታሰቢያ አበባ በድላችን ሀውልት ሲያስቀምጥ
መጣጥፍ – ነፃ አስተያየት
ውስጠ ወይራው ያለመለወጥ ‘ለውጥ’ (በቃሉ ሰውመሆን (የሕግ ባለሙያ)
አቢቹ ሰብሮ የወጣው ወያኔ የጣለውን እቁላል ነው፤ በጥቅሉ ከ 1960 ዓ.ም ወዲህ እስካለንበት በተከሰተው እንዘጭ እቦጭ ውስጥ ኢትዮጵዊነትን ለከፍተኛ ኪሳራ የዳረገ እራስ በል እና እራስበሉን አስቀጣይ የሆነ ሽግግራዊ ክሽፈት አጋጥሞናል፤ አንደኛው የክሽፈት አንጓ የንጉሳዊ ስርአቱን አንጸባራቂ ውርሶች አዘምኖ ማሸጋገር ሲገባ ለአውዳሚ አቢዮት መዳረጋችን ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የኢሕአዴግን አራሙቻ ስርአት የሚነቅል አብዮታዊ የስርአት ለውጥ ማዋለድ ሲገባን More/ተጨማሪ…
አኬልዳማዋ ኢትዮጵያ(ውቤ ደነቀው መኮንን)
ትሕነግ/ኢሕአዴግ ባለፉት ሀያ ሰባት ዓመታት ኢትዮጵያ ሀገራችንን ሊበላትና ሊበታትናት ሲሠራ ቆይቷል:: ሲያስገነጥል ውድ ታጋይ ልጆቿንም ቁም ስቅል ሲያሳይ የነበረው ይህ ቡድን በቆራጥ፣ ግንባራቸውንና ደረታቸውን ለሀገር ሲሉ ራሳቸውን ለጥይት የሰጡት ጀግና ከሕዝብ አብራክ የተገኙ የእማ ኢትዮጵያ ውድ ፍሬዎች በከፈሉት የህይዎትና የአካል መስዋዕትነት የተገረሰሰው ነውረኛና ሆዳም ቡድንን ተከላከልኩ ብሎ አዲስ ለመጣውና ኢትዮጵያን ወደ ሰላምና ዴሞክራሲ ይወስዳል ተብሎ More/ተጨማሪ…
የማንነት ፖለቲካ ምንነትና አደጋዎቹ ባህላዊ ማንነትን ፖለቲከኛ ስናደርግ ያመረትናቸው ችግሮች(ገለታው ዘለቀ )
የማንነት ፖለቲካ ይህን ስያሜውን ያገኘውና በሚታይ መልክ ብቅ ያለው በ20ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ነበር። በዚሁ ወቅት የሴቶች ንቅናቄ፣ የጥቁሮች ንቅናቄ፣ የአካለ ስንኩላን ንቅናቄዎች፣ የብሔር ንቅናቄ በስፋት የታዩበት ጊዜ ነበር። የማንነት ፖለቲካ ወደ አካዳሚክ ዲስኩር የገባውም በዚሁ በቅርቡ ነበር።የማንነት ፖለቲካ ስንልም በእነዚህ ማንነቶች ላይ የሚሰራ የፖለቲካ ቤት ማለታችን ነው። ወደዚህ ፖለቲካ የሚገቡ ሃይሎች ደግሞ የፕራይሞርዳያሊዝም More/ተጨማሪ…
ስር የሰደደው የዐቢይ የተቋም አተካከልና ክትትል ችግር (ገለታው ዘለቀ)
ከሁለት አመታት በፊት በሃገራችን የፖለቲካ ለውጥ የሸተተን መስሎን ስለ ሽግግር ብዙ አልን፤ እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ለውጡ መጣሁ መጣሁ ሲል በፍጥነት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አለብን የሚል ድምጽ አሰሙ:: ይህ ድምጽ ግን በጣም የጥቂቶች ነበር:: አብላጫው ሰው ዶ/ር አብይ የሚመሩት መንግሥት የሽግግሩን ሥራ ይስራው የሚል ነበር:: ለለውጡ በጣም የሳሱ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የዶ/ር አብይን መንግሥት በርታ፣ ጎበዝ፣ More/ተጨማሪ…