ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
አስቸኳይ ማስተካከያ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የ2013 ዓ.ም. ምርጫን አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በራስ አምባ ሆቴል ረፋድ 4፡00 ሰዓት ይፋ ለማድረግ ለመገናኛ ብዙኅን ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።ይሁን እንጂ ባልደራስ ሊሰጠዉ ያቀደው ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግስት አፋኝ ቡድን በመከልከሉ ጥናቱን በተጣበበ ቦታም ቢሆን በቢሯችን ይፋ ለማድረግ ወስነናል።በመሆኑም በተጠቀሰው ሰዓት ስድስት ኪሎ፤ ምስካየኅዙናን መድሀኒያለም More/ተጨማሪ…
የጋዜጣዊ መግለጫ ጥሪ
የሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን ምርጫ በተመለከተ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል አጠቃላይ ውጤት መገለጹ የሚታወቅ ነው።ይህም በመሆኑ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የ2013ን ምርጫ አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም በራሳ አምባ ሆቴል ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይፋ ያደርጋል ። የእለቱን መርሃግብር የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡ ስንል ጥሪ እናቀርባለን ።ከሠላምታ ጋር !
ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ለሃምሌ 29 እነ እስክንድርን በድጋሜ ቀጠረ
አቃቤ ሕግ ከጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ያወጣውን የዕግድ ትዕዛዝ ማህተም አስደርጎ ለ9 ሰዓት “ቀርቢያለሁ” ማለቱን ተከትሎ ነው በድጋሜ ለሐምሌ 29 ቀን 2013 ዓ.ም የተቀጠረው።የፌደራሉ ጠቅላይ ሰበር ሰሚ ችሎት ባወጣው የዕግድ ትዕዛዝ ዙሪያ ሐምሌ 26 /2013 ዓ.ም የግራ ቀኙን ጉዳይ ለመመልከት ቀጠሮ ሰጥቷል።ከፍተኛ ፍ/ቤቱ አቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት በአምስት ቀናት ውስጥ ምስክር እንዲያሰማ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል። More/ተጨማሪ…