ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ለነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ‘የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባና በዝግ ችሎት ይቅረቡ ወይስ በግልፅ ችሎት ይሰሙ’ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ነው። ትናንት ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበረው ችሎት መዝገቡን አለመመርመሩን ጠቅሶ ለዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ማሸጋገሩ ይታወሳል።ይህንኑ የምስክሮች አሰማም ሂደት በተመለከተ More/ተጨማሪ…
ለባልደራስ ክስ ምርጫ ቦርድ ነገ በፍርድ ቤት መልስ ያቀርባል !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ምርጫ 2013 ላይ የተሠሩ ሕገ ወጥ ተግባራትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅሬታዎችን ቢያቀርብም ከሕግ አግባብ ውጭ በማን አለብኝነት ውድቅ ተደርገውበታል። በመሆኑም ጉዳዩን ወደ ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወስዶ በምርጫ ቦርድ ላይ ሕጋዊ ክስ መስርቷል።ፓርቲው ለመሰረተው ሕጋዊ ክስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነገ ሀምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ለፍርድ ቤቱ More/ተጨማሪ…
አስቸኳይ ማስተካከያ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የ2013 ዓ.ም. ምርጫን አጠቃላይ የጥናት/የምርመራ ውጤት አስመልክቶ ነገ ሐምሌ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. በራስ አምባ ሆቴል ረፋድ 4፡00 ሰዓት ይፋ ለማድረግ ለመገናኛ ብዙኅን ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።ይሁን እንጂ ባልደራስ ሊሰጠዉ ያቀደው ጋዜጣዊ መግለጫ በመንግስት አፋኝ ቡድን በመከልከሉ ጥናቱን በተጣበበ ቦታም ቢሆን በቢሯችን ይፋ ለማድረግ ወስነናል።በመሆኑም በተጠቀሰው ሰዓት ስድስት ኪሎ፤ ምስካየኅዙናን መድሀኒያለም More/ተጨማሪ…