ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
ለሚዲያ አካላት የቀረበ ጥሪ !
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ጋር በመተባበር “የምርጫ 2013 ተስፋና ስጋቶች” በሚል ርዕስ በራስ አምባ ሆቴል ነገ ሚያዚያ 07/2013ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ስዓት ጀምሮ ውይይት ያካሂዳል።ዝግጅቱ ለሁሉም የብዙሃን መገናኛ ክፍት በመሆኑ ሁሉም የሚዲያ አካላት በሥፍራው ተገኝተው እንዲዘግቡት ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል።
በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት በዛሬው ችሎት ሊዳኝ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ለሚያዝያ 15 ተዛወረ !!
በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚደረገው ችሎት ለዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀጥሮ የነበረው ችሎት ‘ፕላዝማው ተበላሽቷል’ በሚል ለፊታችን ሚያዝያ 15 ቀን ተዘዋውሯል። ይኸው ችሎት ከዚህ በፊት ለመጋቢት 28 ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን ከሦስቱ ዳኞች መካከል አንዱ ባለመገኘታቸው ነበር ለዛሬ የተሸጋገረው። የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከፕላዝማ ይልቅ በችሎቱ ፊት ለፊት More/ተጨማሪ…