ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
እነ እስክንድር ነጋ ለሚያዝያ 26 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጣቸው
የእነ እስክንድር ነጋን ዶሴ የተመለከተው በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ዛሬ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. የፕላዝማ ችሎቱን አካሂዷል። በዚህም ምስክሮቹ በግልፅ ችሎት ይቅረቡ ወይስ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ካሉበት ወህኒ ቤት ሆነው በፕላዝማ ስክሪን ችሎት የቀረቡት የህሊና እስረኞች ምርጫው ሳምንት ሲቀረውም ቢሆን More/ተጨማሪ…
የችሎት ውሎ
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በማገዱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለዛሬ የቀጠረውን የእነ እስክንድር ነጋን ችሎት ሳይዳኝ ቀረ፡፡ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በቀጠሯቸው መሠረት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ይሁን እንጂ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እያከራከረው በሚገኘው የይግባኝ More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ ከቃሊቲ የላከው መልዕክት!
“ህዝቡ የምርጫ ሰራዊት መሆን አለበት። ይሄ ምርጫ የሚወስነው የአምስት ዓመት፣ የአስር ዓመትን ዕጣ ፋንታ አይደለም የትውልድን እንጂ።ስለዚህ ፣ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ምርጫ ካርድ እንዲወስድ፣ እንዲመርጥና ምርጫውን በታዛቢነት በንቃት እንዲከታተል ጥሪ አቀርባለሁ “ድል ለዲሞክራሲ