ዜና(News)
የሦስት ቀን የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ ጥሪ!
የሦስት ቀን የማህበራዊ ድረ-ገፅ ዘመቻ ጥሪ!” ጳጉሜን ፤ ፍትሕ ለግፍ እስረኞች “አገራችን ኢትዮጵያ በአሁን ወቅት የገጠማት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲን በእጅጉ ያሳስበዋል። በተለይ የወቅቱ የሃገራችን የፖለቲካና ወታደራዊ ሁኔታ አደገኛ ከመሆኑ አንጻር ጉዳዩን በጥንቃቄ በማየት ተገቢውን ውሳኔ መስጠት እንደሚያስፈልግ ከእነ መፍትሄ አሳብ ጭምር ባልዳራስ መግለጹ የሚታወቅ ነው።አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ፤ ህዝባዊ More/ተጨማሪ…
በጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እስር ላይ ሦስት ወር ተቀነሰ !
የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውን ችሎት በመድፈር ጥፋተኛ በማለት በ4 ወር እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ የሚታወስ ነው ።ሆኖም ፤ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የቅጣት ውሳኔ ውድቅ እንዲሆን በቀረበው ይግባኝ መሠረት ፤ይግባኙን የመረመረው ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎች በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተሰጠውን የቅጣት ውሳኔ ሦስት ወር በመቀነስ በአንድ ወር እስራት ውሳኔ ሰጥቷል ።
እነ እስክንድር ነጋ በተከሰሱበት መዝገብ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ታሰረ ! የምስክር አሰማም ሂደት ለጥቅምት ተቀጠረ !
በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፤ ከችሎት ዘገባ ጋር በተያያዘ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ፣ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እንዲሁም አሐዱ ራዲዮ ” የተሳሳተ እና ዘገባ እና ጽሁፍ ” በማቅረቡ እና ችሎት መድፈር ህግ ተላልፋችኋል በማለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፖሊስ በላከው መጥሪያ መሰረት ተጠርጣሪዎች ዛሬ ፍ/ቤት ቀርበዋል።ፍ/ቤቱ More/ተጨማሪ…
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በእነ እስክንድር ነጋ ዶሴ ላይ ለነሐሴ 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠው ‘የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ከመጋረጃ ጀርባና በዝግ ችሎት ይቅረቡ ወይስ በግልፅ ችሎት ይሰሙ’ ለሚለው ክርክር ብይን ለመስጠት ነው። ትናንት ነሐሴ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበረው ችሎት መዝገቡን አለመመርመሩን ጠቅሶ ለዛሬ ነሐሴ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ማሸጋገሩ ይታወሳል።ይህንኑ የምስክሮች አሰማም ሂደት በተመለከተ More/ተጨማሪ…