ዜና(News)
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ !
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442 ኛው የኢድ አል- አዷኻ/አረፋ/ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ምርጫ ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ (#ባልደራስ) ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ባልደራስን ወክለው በምርጫ ጣቢያዎች ለታዘቡ አባላት እና ደጋፊዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ ።በመርሃግብሩ ላይ የባልደራስ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን በምርጫ 2013 አስተዋፅኦ ያደረጉ ታዛቢዎችንያመሰገኑ ሲሆን፤ በመጪዎቹ ጊዜያትም በተጠናከረ መልኩ ከባልደራስ ፓርቲ ጋር በአጋርነት አብረው እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል ። የምስጋና ሰርተፍኬት የተበረከተላቸው More/ተጨማሪ…
ዐቃቤ ህግ ዛሬም ምስክሮቹን በችሎት ፊት ማቅረብ አልቻለም!
ከዛሬ ጀምሮ ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማሰማት እንዲጀምር የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በትላንትናው ዕለት ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ዐቃቤ ህግ ምስክሮቹን ማቅረብ አልቻለም ። ምስክሮቻችንን በ15 እና 16 እናሰማለን እስከዚያ ድረስም ለምስክሮች ጥበቃ የሚያስፈልጉ ተግባራትን አከናውናለው በማለት ዐቃቤ ምስክሮቹን አለማቅረቡን ለፍ/ቤት ተናግሯል ።ይሁን እንጂ የግፍ እስረኞች ጠበቆች ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ምክንያት ውድቅ በማድረግ ። ምስክር አሰማሙ በአምስት More/ተጨማሪ…
በነ እስክክንድር መዝገብ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ምስክር የመስማት ሂደት በዐቃቤ ህግ ምክንያት ቀረ !
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ በዛሬው ዕለት ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል።ከዚህ ቀደም በዋለው ችሎት ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች እንዲሰሙ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት More/ተጨማሪ…