ዜና(News)
ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጧት 3 ሰዓት ላይ ችሎት ይቀርባሉ።በመሆኑም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ላይ በመገኘት ክርክሩን እንድትዘግቡ ባልደራስ ጥሪ ያቀርባል።
ዳኛው የሉም? (ጌጥዬ ያለው)
በእነ እክንድር ነጋ መዝገብ ላይ ከዚህ በፊት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና ሰበር ሰሚ ችሎት “ዳኞች ተሟልተው አልቀረቡም”፣ “መዝገቡን አልመረመርንም”፣ “ፕላዝማ ተበላሽቷል” በሚሉ ሰበቦት እስከ አንድ ወር ድረስ የረዘሙ ተለዋጭ ቀጠሮዎች ይሰጡ ነበር። በዚህም ምክንያት ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይቅረቡ?፣ ከመጋረጃ ጀርባ ይቅረቡ?፣ በዝግ ችሎት ይቅረቡ በሚል ጉንጭ አልፋ ክርክር ሲሟገቱ ከአንድ አመት More/ተጨማሪ…
ችሎት፤ ጥቅምት 5 ቀን 2014
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። ዐቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮችን በግለፅ ችሎት እንዲያሰማም ለዛሬ ከቀትር በኋላ ማለትም ከቀኑ ከ7:30 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል። More/ተጨማሪ…
ችሎት (ጌጥዬ ያለው)
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከአለፈው ዓመት ሐምሌ 14 ቀን በኋላ ዛሬ ጥቅምት 4 ቀን 2014 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በአካል ቀርበዋል። በዓቃቤ ሕግ ጠያቂነት በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታግዶ More/ተጨማሪ…