ዜና(News)
ነገም እንደዛሬው የሞራል ግዴታችንን እንወጣ!
በዛሬው የእነ እስክንድር ነጋ ችሎት ላይ ለመታደም የፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ መጥታችሁ ‘አዳራሽ ሞልቷል’ በሚል ችሎቱን ሳትታደሙ የተመለሳችሁ የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ተቆርቋሪዎች በርካቶች ናችሁ። ከኅሊና እስረኞች ጎን መሆናችሁን ስላሳያችሁን በእጅጉ እናመሰግናለን።ችሎቱን የታደማችሁም ሆነ የተከለከላችሁ አጋርነታችሁን አሳይታቸሰኋልና ፈጣሪ አጋር ይሁናችሁ። የሞራል ግዴታችሁን መወጣታችሁ በታሪክ ተመዝግቦ ለትውልድ እንደሚተላለፍም ተስፋ እናደርጋለን።ችሎቱ ነገም ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. More/ተጨማሪ…
ዐቃቤ ሕግ በእነ እስክንድ ነጋ ላይ የሚቀርቡ ምስክሮች ዝርዝር በሚዲያ እንዳይቀርብ ያቀረበውን አቤቱታ ፍ/ቤት ውድቅ አድርጎታል
በዚህም መሰረት ፦በነ #እስክንድር ነጋ ላይ ከነገ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በግልፅ ችሎት እንዲመሰክሩ ዐቃቤ ሕግ የዘረዘራቸው ሰዎች ስም ዝርዝር:-1. ፈንታሁን አሰፋ2. መንበረ በቀለ3. ወርቁ ታደሰ4. ፍፁም ተሰማ5. ደረጀ ግዛው6. ቴዎድሮስ ለማ7. ያየህ ብርሃኑ8.ጌትነት ተስፋዬ9. ትንሳኤ ማሞቀሪ የ12 ምስክሮች ስም ዝርዝር ነገ ጧት እንዲቀርብ ታዝዟል። ከላይ ከተጠቀሱት መካከል ሁለቱ ነገ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ ተብሎ More/ተጨማሪ…
የችሎት ክለሳ
ጌጥዬ ያለውየፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ.ም. የእነ እስክንድር ነጋን መዝገብ ቁጥር 260175 ገልጦ የይስሙላ ክርክሩ ቀጥሏል። ባለፈው ጥቅምት 5 ቀን በተቀጠረው መሰረት ዐቃቤ ሕግ በግልፅ ችሎት እንዲያቀርባቸው የታቀዱ ምስክሮች ስም ዝርዝር ለመገናኛ ብዙሃን፤ በተለይም ከሳሽ እንደ እንኩሽ በሚፈራው ፌስቡክ ይገለፅ More/ተጨማሪ…
ለሀገርና ለህዝብ መብትና ጥቅም በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ ለታሰሩት ድምጽ እንሁን!
ከአንድ አመት በላይ በግፍ እስርቤት ለሚገኙት የዘመናችን የሰላት ታጋይ እንቁዎች እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እንዲሁም አስካል ደምሌ ከእስር እንዲፈቱ የሞራል ግዴታችንን እንወጣ !ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 9, 2014 ዓ. ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንገናኝ።