ዜና(News)
6ኛው ሃገራዊ ምርጫ እንዲታገድ ባልደራስ ፍርድ ቤትን ጠየቀ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ከፍተኛ አመራሮች ፤ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ ፤በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር በዕጩነት እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።በውሳኔው መሰረት ምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽም ባልደራስ በደብዳቤ የተጠየቀ More/ተጨማሪ…
ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም አለ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ ውሳኔ More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ፓርቲ አማራጭ የኢኮኖሚ ሞዴል
ዜጎች በተፈጥሮ እኩል በመሆናቸው የሰብዓዊ እንዲሁም የዜግነት መብታቸው መከበር አለበት፡፡ ተዘዋውሮ የመስራት፣ የመወሰን፣ ሀብት የማፍራት፣ በተገቢው ፍትሕ የመዳኘት እንዲሁም ንቁ ተሳትፎ የማድረግ እኩል ዕድል እና መብት አላቸው፡፡ በዘር፣ በቀለም፣ በሀብት፣ በጾታ፣ በሀይማኖት፣ በአመለካከት፣ ወዘተ. ላይ የተመሰረተ አድልዎ ተገቢ አይደለም ብሎ ባልደራስ ያምናል። አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ከተማ ናት ሲልም በዚሁ የማያወላውል መርሑ እና ፅኑ እምነቱ More/ተጨማሪ…
እነ እስክንድር ነጋ ለመጪው ምርጫ በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ የሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ
በቅድስት ሙላቱየፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ሰበር ሰሚ ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቀለብ ስዩም እና አስካለ ደመሌ ለፓርቲው በእጩነት ተመዝግበው መወዳደር እንደሚችሉ ውሳኔ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ዛሬ ሰኞ ግንቦት 16 በነበረው የችሎት ውሎው ነው።ችሎቱ ውሳኔውን የሰጠው የባልደራስ ፓርቲ አመራሮችን በተመለከተ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተላለፈውን እና በስተኋላ More/ተጨማሪ…