ዜና(News)
የሐዘን መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስክንድር ነጋ !
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት በተመለከተ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት የሐዘን መልዕክት ።”መካሪዬ፣ አባቴ፣ አስተማሪዬ የሆኑት በማረፋቸው በጣም አዝኛለሁ። ጓጉተውለት የነበረውን የዘንድሮ ምርጫ ውጤት አይተው ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃዱ አልሆነም። የሰላም እረፍት ይሁንላቸው። ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ”እስክንድር ነጋከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት
አስቻይ ሁኔታዎች በሌሉበት የሚከናወን ምርጫ ሀገር በጉጉት ወደምትጠብቀው ሥርዓት አያሸጋግርም !
በሕብር ኢትዮጵያ፣በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣በባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፣በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እናበእናት ፓርቲበጋራ የተሰጠ መግለጫሀገራችን ኢትዮጵያ የምታካሂደው ስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ፍትህ፣ እውነተኛ ዲሞክራሲና ሠላም የራቀው ህዝባችንን አንድ እርምጃ ወደፊት በማራመድ በዚህ አቅጣጫ በምናደርገው ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ከፋች እንደሚሆን በማመን በምርጫው ሂደት ከመነሻው ጀምሮ የጎላ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንገኛለን፡፡በታሪኳ ተዓማኒነት ያለው ምርጫ አካሂዳ ለማታውቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ ምርጫው More/ተጨማሪ…
ለ1997 ዓ.ም. ሰማዕታት ቋሚ መታሰቢያ ይቁምላቸው!
ያለፈው ይብቃ!ለ1997 ዓ.ም. ሰማዕታት ቋሚ መታሰቢያ ይቁምላቸው!ባለፈው አመት ልክ በዛሬዋ ቀን የዚህን ተመሳሳይ መግለጫ አውጥተናል። ዛሬም እንደግመዋለን፤ የ1997 ምርጫ ሰማዕታትን ሁልጊዜም ስናስታውሳቸው እንኖራን። እንደ አምናው ሁሉ ዘንድሮም ቋሚ መታሰቢያ እንደመቆምላቸው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ይጠይቃል።1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያውያን ዘንድ በዘመናት መካከል የማይረሳ ጊዜ ነበር፡፡ እልፎች ኢትዮጵያውያን የንጋት ምልክት ያዩ መስሏቸው ለምርጫ የወጡበት ጊዜ ነበር፡፡ ይሁን More/ተጨማሪ…
በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በሴት ዕጩዎች ብቻ የተመራ የምርጫ ቅስቀሳ !
” አዲስ አበባን ራስ ገዝ አስተዳደር እናደርጋታለን !”ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ የባልደራስ-ሴት-አባላት-ቅስቀሳ