ዜና(News)
ሀገር ወዳዱ የአዲስ አበባ ሕዝብ ሆይ !
ነገ የካቲት 14 እግሮች ሁሉ ወደ መስቀል አደባባይ ያቀናሉ !ከተማህን የመምረጥ፣ የማስተዳደር እና የመወሰን ሥልጣንህን የማስመለስ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርግ ባልደራስ ለእዉነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጥሪውን ያቀርባል።የአዲስ አበባ ህዝብ ተስፋ የሆነው ባልደራስ የ2013 ዓ.ም የምርጫ ቅስቀሳ ጀምሯል።
ባልደራስ ከውጪ ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያየ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዲስ አበባ ከሚገኙ የተለያዩ የውጪ ሃገራት አምባሳደሮች ጋር በራዲሰን ብሉ ሆቴል በወቅታዊ ጉዳዬች ላይ ተወያዩ፡፡ መጪው ሃገር አቀፍ ምርጫ፣ የባለደራስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ህገወጥ እስር ፣በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ዜጎች በሐይማኖታቸውን እና በማንነታቸው እየተለዩ በሚደርስባቸው ሞት እና መፈናቀል በተመለከተ ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ አሁን የታዩ More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች እና አባላት በሰማዕታት የመታሰቢያ ሀውልት የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ
በዛሬው እለት የካቲት 12/ የሰማዕት ቀን ምክንያት በማድረግ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አመራርና አባላት ስድስት ኪሎ በሚገኘዉ የጀግኖች ሰማዕታት የመታሰቢያ ሐዉልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል። በባለፈው ዓመት የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝደንት እስክንድር ነጋ ለጀግኖች ሰማዕት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ፤ በቦታው ለተገኙ የሚዲያ አካላት ” ባልደራ በምርጫ አሸንፎ ህዝብ እዱሉን ከሰጠዉ ይህንን ቀን እጅግ በጎላ More/ተጨማሪ…
የካቲት 12፤ እየወደቁ የማሸነፍ ተምሳሌት
(የህሊና እስረኛው ስንታየሁ ቸኮል ከቃሊቲ ወህኒ ቤት ያስተላለፈው መልዕክት) አገር ወዳዶቹ አብርሐ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በግራዚያኒ ላይ በሠሩት ጀብዱ ከ30 ሺህ በላይ ወገኖቻችን ወድቀዋል። የካቲት 12 የሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ነው። ነገር ግን የካቲት 23 ደግሞ የድል ቀን ነው። የአድዋ ቀን ነው። የማሸነፍ ቀን ነው። እየሞቱ ማልቀስ ብቻ ሳይሆን እየወደቁ ድል እንዳለ አድዋ ምስክርነቱን ሰጥቷል። እንደ More/ተጨማሪ…