ጥናታዊ ጽሁፍ
ዜና
በአፍራሾቿ ዶማ ላይ የተኛችው አዲስ አበባ (ጌጥዬ ያለው)
አንድ ተረት አለ፤ ትዝ የሚለኝ፡፡ ሁለት ወንዶች በአውድማ ተኝተው ነው፡፡ በውድቅት ሌሊት ጅብ መጣና የአንደኛውን እግር እንደሸንኮራ አገዳ ሞሽልቆ መቆርጠም ጀመረ፡፡ ጓደኛው ድምፅ ሰምቶ ምን እየሆነ እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ፈሪው ጓድ ‹‹ጅብ ነው፡፡ ተወው እግሬን ብቻ ነው የሚበላው›› አለው ነው ተረቱ፡፡ ‹‹ታዲያ እግርህን ከበላው ነፍስህንም እንዳይበላት ይሆን የምትጨነቀው?›› በማለት ጅቡን አባረረው፡፡ ፈሪውም አንካሳ ሆኖ ቀረ፡፡ በሰሞኑ More/ተጨማሪ…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆች የቀረበው አቤቱታ ላይ ፍ/ቤቱ፣ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።ጠበቆቹ በብይኑ ላይ ቅሬታ ስላደረብን ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን በማለት የህግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ More/ተጨማሪ…
የሐዘን መልዕክት ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እስክንድር ነጋ !
የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሊቅ፣ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ሕልፈተ ሕይወት በተመለከተ የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዚደንት የሐዘን መልዕክት ።”መካሪዬ፣ አባቴ፣ አስተማሪዬ የሆኑት በማረፋቸው በጣም አዝኛለሁ። ጓጉተውለት የነበረውን የዘንድሮ ምርጫ ውጤት አይተው ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ፈቃዱ አልሆነም። የሰላም እረፍት ይሁንላቸው። ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓደኞቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ”እስክንድር ነጋከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት