ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

About Us | Contact Us | Sitemap |
April 17, 2021

ኢ/ጅ ቢኒያም መልሳቸው

ኢንጅነር ቢኒያም መልሳቸው

#በልደታ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 3

አዲስ አበቤ በልጆችህ ስነ-ልቦናህን በአግባቡ በሚያውቁልህ እንደራሴዎች ለመወከል ያለህ ትክክለኛ አማራጭ ጊዜው አሁን ነው !!

ኢንጅነር ቢኒያም መልሳቸው እባላለሁ። በሙያዬ መሃነዲስና ኢንተርናሽናል ትሬድ ኢኮኖሚስት ነኝ። የምወዳደረውም በልደታ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 3 ላይ ነው፡፡ የመማር፣ የማወቅ እና የማሰላሰል ጥቅሙ ምንድን ነው የሚል የረጅም ጊዜ ሙግት በህሊናዬ ውስጥ ይመላለስ ነበር፤ የሶስቱም የመዝገበ ቃላት ፍቺ ባውቃቸውም አሁን የሃገራችን ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያዊነት ማጠንጠኛ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ ላይ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ከላይ የጠቀስኳቸው ሶስት የግንዛቤ ጥያቄዎች ለመመለስ እና ከሌለው የኑሮ ጉርሱ ላይ በውዴታ ግዴታ አበርክቶ እኔን ለዚህ ላደረሰኝ ማህበረሰብ እነዚህ ጥያቄዎች በተጨባጭ ከተማርኳቸው የትምህርት መስኮች እንዲሁም ከቀሰምኩት የህይወት ልምድ በተጨማሪም ካየሁት ከሰማሁት ካነበብኩት እንዲሁም ከኖርኳቸው ቁጭትን ከሚፈጥሩ የፖለቲካ አሻጥሮች ፣ መገፋቶች እና በደሎች ጋር ተዳምሮ የመማርን የማወቅን እና የማሰላሰልን ተጨባጭ ሃቅ ላደኩበት ማህበረሰብ የህዝቤን ቁመና በሚመጥን መልኩ ማበርከት እንዳለበኝ ስለተሰማኝ በቀጥታ ተሳትፎ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲን በመቀላቀል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመመረጥ እጩ ሆኛለሁ።

ባለፉት 5(አምስት) አገራዊ ምርጫዎች የከተማዬ ህዝብ አንድም ጊዜ ራሱ በመረጠው የህዝብ እንደራሴ ተወክሎ አያውቅም፡፡ የማህበረሰቡን ስነ-ልቦና በማያውቁ ምስለኔ ገዥዎች እያፈራረቁ ለከፍተኛ የፖለቲካ የኢኮኖሚ እንዲሁም ለዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች ለፍትህ እጦት ሲዳርጉት ዘመናት ተቆጥረዋል።

በበታችነት የፖለቲካ እሳቤ ዘውጌ የከተማው ህዝብ ለዘርፈ ብዙ በደሎች አሳልፈው ሰጥተውታል። በመሆኑም አዲስ አበቤ በልጆችህ ስነ-ልቦናህን በአግባቡ በሚያውቁልህ እንደራሴዎች ለመወከል ያለህ ትክክለኛ አማራጭ ጊዜው አሁን በመሆኑ ካርድህን በማውጣት ከፊትህ የተጋረጠብህን የዳግም የምስለኔ አስተዳደር እምቢኝ ማለት ይገባል።

እኔም ያደኩበትን ማህበረሰብ እንደሚያውቅ ግለሰብ ብመረጥ ለፍትህ ለነፃነት ለእኩል ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ለፖለቲካዊ ውክልና በከፍተኛ ደረጃ ኢትዮጵያዊ ስነ-ምግባርን እና የአዲስ አበቤን ቅንና አራዳ የሆነ ስነ-ልቦናን በመላበስ እስከ መጨረሻው ላገለግልህ እንደምፈልግ ስገልፅ በታላቅ አክበሮት ነው።

ሁላችሁም ግንቦት 28 አዲስ አበቤና ባልደራስ የጋብቻ ቀናቸው ስለተቆረጠ ከአሁኑ ካርዳችሁን በመያዝ ለሰርጉ ተጠርታችዋል፡፡

ያሳደጋችሁት ልጃችሁ ነኝ ኢንጅነር ቢኒያም መልሳቸው።

ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ !!!

ኢ/ር ጌታነህ ባልቻ ዶ/ር ቴዎድሮሥ ኃይለማርያም

Related Posts

እጩ ተወዳዳሪ

አዲሱ ሀረገወይን

እጩ ተወዳዳሪ

መምህር ተሰማ አያሌው

እጩ ተወዳዳሪ

ዶ/ር ብርሃኑ ዘለቀ

Recent Posts

  • የባልደራስ ድጋፍ ሰጪ በሰሜን አሜሪካ October 23, 2021
ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

ድል ለዲሞክራሲ!!!

© ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ Balderas for true democracy 2021