ግጥም(Poem)
አወይ እኔነቴ (በቃሉ ሰውመሆን)
ጅምሬ ቀዳሚጉዞዬ አድካሚውጣ ውረድ ያለውከሚዛኑ ዝንፍ ወይፍንክች የሌለውከአፈር በቅዬበአፈር አብቅዬአፈር እየገፋው አፈር የሚገፋኝአፈር እየበላው አፈር የሚበላኝማብቀያም ዘርም ነኝበአንድነቴ ውስጥ ህብረ-ቀለም ያለኝሀዘኔን፣ ደስታዬን የምቋጭ በስንኝየዘመን ውዥምብር የማይሸረሽረኝባቋሜ ጸንቼ በቃሌ የምገኝሲጠልፉኝ አቅንቼ ሲገፉኝ የምሸኝ ቀለምን ጠንቅቄ በቃሌ እምወጣከምንጩ ቀድቼ ከምንጩ እምጠጣበሀሳብ ወጥኜ በምግባር ተስዬ በግብር የምወጣየተላለፈኝን አይቀጡ ምቀጣየተማመነኝን ፍቅር የማጠጣአወይ እኔነቴከጥንቱ ቀድቼ የነገን ማስላቴየማይመነዘር ዝንጉርጉርነቴምናቤ እምቅ ንግግሬ More/ተጨማሪ…
ታሪክ ምስክር ነው (ውቤ ደነቀው መኮንን)
ይላል የቀድሞ ሰው ጉድ ነው የፍንጅርቱእናቲቱን አንች ልጅዬውን አንቱማድረጉ ሲገርመው ሌንጮን አማካሪ እስኬውን ታሳሪብሎ እያጠየቀ የመሪ ተግባር ነው? ወይስ የመሰሪ?እንግዲህ ኢትዮጵያ ጠንክረህም ታገል ከችግር ተማርባልደራስ መጣልህ እራሱነን ፈቶ ፍፁም ነፃወጥቶ ከህሊና እስር በፍፁም ተላቆ ከፍርሃት ቆፈንመሪውን አድርጎ ታላቅ እስክንድርስንታዬው ይልሃል አሻግሮ ሲያማትርቀለቡን ሰንቆ ወንዝ የሚሻገርበአስካል በፀዳሉ ተውቦ በሀገርበትግል ጠንክሮ ምርጫን አሸንፎ ሊያፀና ሀገርይመስገን ይወደስ ከባደረቦቹ More/ተጨማሪ…
ለእስር ያላት ብዕር (ርብቃ አብርሐም)
ከፅንሰት እስከ ልደት፣ከእድገት እስከ እውቀት፤ሰብዓዊነት እኩልትን – በመርህ ብትፅፍ፣ለአንድነት ህብረት – ቆርጣ ብትሰለፍ፣ሌብነት ጭቆናን – አድሎን ብትፀየፍ፣ዘረኝነት ልዩነትን – የአንባገነንን ግፍ፤በሰላም በታገለች፣አምርራ በሞገተች፣ዘብጥያ ተጣለች።ለውይይት ድርድር – የቆረበች ታጋይ፣ለሕዝቦቿ ታማኝ – ቃል ለምድር ሰማይ፤ስነ-ልቦናዋ – ለትውልድ የሚተርፍ፣ሰንደቅ ያነገበች – የነፃነት ደጃፍ፣ለፅኑ ዓላማዋ – ህሊናዋ ማይነጥፍ፣‹ክልል› ለምኔ – ኢትዮጵያን ብታገዝፍ፤ቃሊቲ ወረደች፣ቂሊንጦ ታሰረች፣ሽብርተኛ ሆነች።ለእስር ያላት ብዕር – ምታነባ More/ተጨማሪ…
የድንጋይ ሽበት (በቃሉ ሰው መሆን)
የድንጋይ ሽበትእስኪ ልጠይቅሽ እውቀት ተናገሪገድ ነሽ መሰጠት ወይንስ መርማሪጨለማውን ገላጭ ብርሀን አብሳሪየተቆለፈውን ሚስጥርን ሰርሳሪ፤በዘመን ዥረት ውስጥ ጥበብ አቀባባይበትናንቱ በኩል የዛሬውን ሁነሽ የነገን የምትስይበዘመን ፍሰት ውስጥ እየተጠራቀምሽጥልመቱን ድቅድቁን ድንቁርናን ገርሳሽእስኪ ልጠይቅሽ እውቀት ተናገሪለመድሽ ወይስ ነሳሽ ዋጥሽ ሳትመረምሪበመጠይቅሽ ላይ መጠይቅ ደራርበሽበውዝግብ ዓለም በመንታ መንገድ ላይ ቀጠልሽ እንደዋለልሽወይስ መልስ አገኘሽ ለጥያቄዎችሽእስኪ ልጠይቅሽ እውቀት ተናገሪጉዞሽ እንዴት ነበር ቁልቁለት More/ተጨማሪ…