ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
መንግስታዊ ሽፋን የተሰጠው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና የምርጫ ቦርድ አሻጥር አስመልክቶ ከባልደራስ የተሰጠ የአቋም መግለጫ !
1ኛ. ከሁሉ አስቀድመን፣ በአገራችን ምዕራብ ኦሮምያ ክልል፣ ወለጋ ውስጥ፣ በሆሮጉድሩ ወረዳ ውስጥ ከየካቲት 27 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ ጥቃት ከ60 በላይ ንጹሃን ዜጎች በኦህዴድ/ብልጽግና ይሁንታ እና በኦነግ ሸኔ አድራጊነት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ የተሰማውን ጥልቅ ኃዘን ባልደራስ ይገልጻል፤ የሟቾችን ነፍስ ፈጣሪ በአጸደ ገነት ያኑርልን፡፡ ለውድ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ፓርቲያችን በአማራ እና More/ተጨማሪ…
መንግሥት በአማራ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ እንዲቆም እንጠይቃለን!
በኦሮሚያ፤ ሆሮጉድሩ ወለጋ አቤ ደንጎሮ አማራዎች ካለፈው ቅዳሜ የካቲት 27 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ እንደ አዲስ በነሲብ እየተገደሉ ነው። የሚገደሉትም በመንግሥታዊ የእዝ መዋቅር በታገዘ ታጣቂ ቡድን ነው። ከግድያ የተረፉት ታግተው ወደ ጫካ ተወስደዋል። ሕፃናት እየታነቁ ወንዝ ውስጥ መወርወራቸውንም ከአካባቢው የወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ። በጉጂ፤ አማሮ ተመሳሳይ ብሔር ተኮር ጥቃቶች እየተፈፀሙ ነው።በመሆኑም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) More/ተጨማሪ…
ለእውነተኛ ፍትህ የሚጨነቅን ሰው በፍትህ ዕጦት ማስጨነቅ የግፍ መጨረሻ ነው !!
የባልደራስ ለዕውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ባልተገኙበት ጠቅላይ ፍ/ቤቱ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱ ተገቢነት የለውም።አቃቤ ሕግ ምስክሮችን በግልፅ ችሎት አቅርቤ ምስክር ማሰማት አልችል በማለት ሰበብ መሪዎቻችን የተፋጠነ ፍትህ እንዳያገኙ እየሰራ መሆኑን ከጅምሩ ፓርቲያችን ይረዳል።ጠ/ፍ/ቤቱ የቀጠሮ ቀን ከመወሰኑ አስቀድሞ የመከራከሪያ ጭብጡን ግልባጭ ጠበቆቻችን በተደጋጋሚ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም ምላሽ ሳያገኙ More/ተጨማሪ…
እንኳን ለ43ኛው የካራማራ የድል በዓል አደረሠን!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ለካራማራ ጀግኖች መታሰቢያ አበባ በድላችን ሀውልት ሲያስቀምጥ