ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
ሀገርን የማዳን ጥሪ – የመጨረሻው መጀመሪያ
ከባልደራስ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተሰጠ ሀገርን የማዳን ጥሪ (Balderas Support in North America )ለብዙ ሺህ አመታት በአባቶቻችን መስዋዕትነት የቆየችው ሀገራችን ዐይናችን እያየ እጃችን ላይ ሳትፈርስ ሁላችንም በአንድ ላይ ልንቆም ይገባል!የተከበራችሁ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ እኛ ኢትዮጵያዊያን የዛሬ ሦስት ዓመት በአገራችን የተካሄደው ለውጥ በልባችን ውስጥ ሰንቆት የነበረው ተስፋ ከህሊናችን በቀላሉ የሚጠፋ More/ተጨማሪ…
የሀዘን መግለጫ
ባለፉት ሁለት ቀናት በሰሜን ሸዋ መንግስት-መር በሚመስል መንገድ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ ጥልቅ ሀዘን የተሰማው ሲሆን በተሰማን ጥልቅ ሀዘን ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ምንም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም እንደማይኖር ማሳወቅ እንወዳለን፡፡ በሞት ለተለዩን ወገኖቻችን ፈጣሪ እረፍትን እንዲሰጣቸው እየተመኘን፤ ለተጎዱ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን፡፡
የሀዘን መግለጫ !
በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል ዕጩ በአቶ በሪሁን አስፈራው ላይ በመተከል ዞን በለስ ልዩ ቦታው ካርባር የተደረገውን የግድያ ወንጀል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ እጅጉን እንደሚያወግዘው እየገለፀ ለሟች ቤተሰብ እና ለባልደርቦቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን የማፍረስ ዘመቻ ይቁም!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በአፋር አርብቶ አደር ወገኖቻችን ላይ በተፈፀመው ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል። ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የአፋር ብሎም የኢትዮጵያ ሕዝብ መፅናናትን ይመኛል። ኦሕዴድ/ብልፅግና ኢትዮጵያን ከቻለ አፍርሶ በራሱ ቀለም እንደገና ለመሥራት ይህ ካዳገተውም እንደ ሐረሩ የራስ መኮንን ሀውልት አፈራርሶ ለመተው እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እናምናለን። ቅርሶችን ጨምሮ ነባር የኢትዮጵያ መገለጫዎችን የማፍረስ እና አንዳዶችን በአዲስ የመተካት More/ተጨማሪ…