ዜና(News)
የእስክንድር እግር መሰበሩ በህክምና ተረጋገጠ !
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በዕቅድ የተደበደበው እስክንድር ነጋ፣ ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ በፖሊስ ሆስፒታል በተደረገለት ህክምና ፣ በግራ እግሩ ላይ ያለው አውራ ጣቱ መሰበሩ በራጂ ተረጋግጧል።በዚህም መሠረት፣ ለሚቀጥሉት ስድስት ሳምንታት የሚቆይ ጄሶ ተደርጎለታል።እስክንድር ከማረሚያ ቤት ሆኖ ባስተላለፈው መልዕክት፣ “በሰሜን ያለውን ጦርነት አስባለሁ። የታሰሩትን አባሎቻችንን አስባለሁ። አጥንታችንን መስበር ይቻላል። ትግላችንን ግን መስበር አይቻልም More/ተጨማሪ…
በጅምላ ከታሰሩት መካከል ሁለቱ በዋስ ሲለቀቁ 40ዎቹ ለሰኞ ተቀጠሩ !
የእነ እስክንድር ነጋን የችሎት ውሎ ለመታደም የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በጥቅምት 11/2014 ዓ/ም የሄዱ 42 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በትላንትናው ዕለት በፓሊስ ታፍሰው መታሰራቸው ይታወቃል።አቶ እስክንድር በእስር ቤት የደረሰባቸውን ድብደባ በችሎት የሰሙ ታዳሚዎች እያለቀሱ ችሎቱን አቋርጠው የወጡ ሲሆን ፤ ከችሎት ወጥተው በመንገድ ላይ More/ተጨማሪ…
በአቶ እስክንድር ነጋ ላይ ስለተፈጸመው ከባድ ድብደባ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠን እንጠይቃለን!!!
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ በሚኖሩበት ቂሊንጦ ወህኒ ቤት ውስጥ ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም. ንጋት 12፡20 ደቂቃ ላይ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ከአቶ እስክንድር ነጋ ጋር አብረው በእስር ላይ ያሉት የፓርቲው የአደረጃጀት ጉዳዮች ሓላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በነበረው የፍርድ ቤት ቀጠሮ የተገኙ ሲሆን የባልደራስ More/ተጨማሪ…
መረጃ ! በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል
በእስክንድር ነጋ ላይ በማረሚያ ቤት ድብደባ ተፈጽሞበታል ። በዚህም ምክንያት ጉልበቱ መቁሰሉን ዋና ሳጅን መስፍን ይልማ የተባሉ የቂሊንጦ ወህኒ ቤት የፈረቃ ሓላፊ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል! በዛሬው ዕለት እስክንድር ነጋ ችሎት መቅረብ አልቻለም ።ይህም በመሆኑ በተከታታይ ምስክር የመስማት ቀጠሮ ተሰርዞ ፤ ለፊታችን ሰኞ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ተዘዋውሯል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ ችሎት ለመታደም የተገኙ በጅምላ ታፍሰው More/ተጨማሪ…