ጋዜጣዊ መግለጫ/PRESS RELEASE
የወቅቱን የሃገራችንን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ሁኔታ በማስመልከት ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በእርስ በርስ ጦርነት ፣ በርሃብ፣ የነገድ ፖለቲካ ባስከተላቸው ቀውሶች፣ በፍትህ እጦት፣ በኑሮ ውድነት፣ ወዘተ… እና በሌሎችም አሳዛኝና አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ከገጠሟት እጅግ አስከፊና አሳዛኝ ወቅቶች መሃከል ይህ አሁን ያለንበት እንደ አንዱ ሊቆጠር ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ምዕራባውያን ሀገራት ከረጅም ጊዜያት አንስቶ ኢትዮጵያን በእነሱ ተጽዕኖ ሥር ለማድረግ ‹‹አማራን ማዳከም ይገባል›› More/ተጨማሪ…

” የምርጫ ውጤቱ ተቀባይነት የለውም። ድምፅ ተዘርፏል”
የስድስተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተለይ የአዲስ አባባ የቅድመ ምርጫ ሂደት እና የድህረ ምርጫ የነጻ፣ የፍትሃዊነት እና የዴሞክራሲያዊ መመዘኛዎችን የማያሟላ መሆኑን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አስታውቋል። “ገዥው ፓርቲ በዋና ፈፃሚነት፤ ምርጫ ቦርድ በተባባሪነት ዘርፈውታል። ይህም በመሆኑ በፍርድ ቤት ክስ መስርቻለው” ብሏል ፓርቲው ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የምርመራ ውጤት። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ More/ተጨማሪ…
በምርጫው ጉዳይ ላይ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ !
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ/ም የተደረገውን 6ኛ አገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ሂደት በተመለከተ መረጃዎችን በአዲስ አበባ ከተማ ካሉ የምርጫ ክልሎች በሙሉ በማሰባሰብ አጠናክሮ ለህዝብ ይፋ ለማድረግ በሚያስችል ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ፣ በድምጽ አሰጣጡ እና ቆጠራው የነበሩ ችግሮችን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ፓርቲያችን አቅርቦ ምላሽ በመጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡ More/ተጨማሪ…
ኢትዮጵያ መቼ ይሆን ነፃ፣ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የሚኖራት ?!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ ፍትህ እንዲሰፍን ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ፣ አድሎአዊነትና ዘረኝነት እንዲወገድ፣ሕዝብ ከመፈናቀልና ከድህነት እንዲላቀቀቅ፣ አዲስ አበባ የራስ ገዝ አስተዳደር እንድትሆን እና ሌሎችም ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲሰፍኑ የሚያስችል ሥርዓት ለማምጣት ጠንክሮ ሠርቷል፤እየሰራም ነው፡፡የሃገሪቱ መሪ ‹‹ከባልደራስ ጋር ግልጽ ጦርነት እንከፍታለን›› እያሉ በተናገሩበት ወቅት እንኳን ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከመታገል ቁርጠኛ አቋሙ ወደ ኋላ አላለም፡፡ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ More/ተጨማሪ…