ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

About Us | Contact Us | Sitemap |
December 21, 2022

የግፍ እስረኞቹ አቶ ካሳሁን ደስታ እና አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ነገ እና ከነገ ወዲያ ፍ/ቤት ይቀርባሉ

 
በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ባለፈው ታህሳስ 06/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ችሎቱም ተጨማሪ 7 ቀናትን ሰጥቶባቸው ነበር። በዚህም መሰረት ነገ ሀሙስ 13/04/2015 ዓ.ም በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የሚቀርቡ ይሆናል።
 
ሌላው በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ የምክር ቤት አባል እና ንቁ ተሳታፊ የሆኑት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ በ05/04/2015 ዓ.ም ፍ/ቤት መቅረባቸው ይታወሳል። ችሎቱም ፖሊስ ከጠየቀባቸው 14 ቀናት የምርመራ ጊዜ ዘጠኝ ተጨማሪ ቀናትን ፈቅዶ ነበር። በዚህም መሰረት ከነገ በስቲያ (አርብ ታህሳስ 14/2015 ዓ.ም) በአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይቀርባሉ።
 
ሁለቱም የግፍ እስረኞች የተከሰሱት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ት/ቢሮ አማካኝነት በህገወጥ መንገድ የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ በአዲስ አበባ ት/ቤቶች መሰቀልንና፣ የኦሮሚያ ክልል መዝሙር መዘመርን ተከትሎ በተማሪዎች፣ በመምህራን እና በወላጆች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ መርታችኋል እና አስተባብራችኋል በሚል ነው።
ፍትህ ለፖለቲካ እስረኞች!
ድል ለዲሞክራሲ!
#ባልደራስ #አዲስ_አበባ #ኢትዮጵያ
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ የግፍ እስረኛው አቶ ካሳሁን ለይደር ተቀጠሩ

Related Posts

ሁለቱም የግፍ እስረኞች ለ ታህሳስ 19 ተቀጠሩ

ዜና

ሁለቱም የግፍ እስረኞች ለ ታህሳስ 19 ተቀጠሩ

የግፍ እስረኛው አቶ ካሳሁን ለይደር ተቀጠሩ

ዜና

የግፍ እስረኛው አቶ ካሳሁን ለይደር ተቀጠሩ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

ዜና

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

Recent Posts

  • ሁለቱም የግፍ እስረኞች ለ ታህሳስ 19 ተቀጠሩ December 26, 2022
ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

ድል ለዲሞክራሲ!!!

© ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ Balderas for true democracy 2021