ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

About Us | Contact Us | Sitemap |
December 14, 2022

በግፍ እስር ላይ የሚገኙት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና አቶ ካሳሁን ደስታ እስር ህገ ወጥ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ እንዲፈታቸው ባልደራስ አበክሮ ያሳስባል

 
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና የፓርቲው ንቁ አባልና ጉዳይ አስፈፃሚ አዲስ አበባ ውስጥ ትላንት ህዳር 03/2015 ዓ.ም. በፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል፡፡ በቅድሚያ የታሠሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ሲሆኑ ለእሳቸው ስንቅ ለማቀበል አቶ ካሳሁን ደስታ በሄዱበት ወቅት እሳቸውንም ፖሊስ አስሮ አስቀርቷቸዋል።
 
የአዲስ አበባ መሥተዳድር እና የኦህዴድ/ብልጽግና መር መንግሥት ቆሜለታለሁ ከሚለው ህገ መንግሥቱ ከሚደነግገው ውጭ የአዲስ አበባ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የኦሮሚያ ክልል ባንዲራ እንዲሰቅሉና የኦሮሚያ ክልል መዝሙርን እንዲዘመሩ ሲያስገድዱ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ ተቃውሟቸውን እየገለጹ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህ ሰላማዊ ተቃውሞ እየተደረገ ያለው ደግሞ በማንም ፓርቲ ቀስቃሽነት ሳይሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ በገዥው ፓርቲ እየደረሰበት ባለው አስከፊ ጭቆናና በደል ምክንያት ብሶትና ምሬት ተሰምቶት በራሱ አነሳሽነት የሚያካሂደው መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡
 
የኦህዴድ/ብልጽግና መንግሥት ከዚህም በፊት ሲያደርገው እንደቆየ ሁሉ አሁንም የባልደራስ ፓርቲን የጦስ ዶሮ በማድረግ አባላቱን ማሰርና ህጋዊ የፓርቲ እንቅስቃሴውን ማወክ ቋሚ ተግባር አድርጎ ይዞታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የባልደራስ ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤውን ለማካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት በሚያከናውንበት ወቅት ያለምንም በቂ ምክንያትና መረጃ አባሎቻችንን በህገወጥ መንገድ በፖሊስ ጣቢያ ማሰርና ማሰቃየት ጉባኤውን እንዳያደርግ እንቅፋት ለመፍጠር እየተደረገ ያለ ሸፍጥ መሆኑ መገንዘብ አስቸጋሪ አይሆንም፡፡ ስለዚህም የኦህዴድ-ብልፅግና መራሹ መንግሥት ይሄን ቆሜለታለሁ ከሚለው ህገ መንግስት ከሚደነግገውና ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ፍላጎት ውጭ በኃይል እየተገበረ ያለውን ድርጊት እንዲያቆም ባልደራስ ያሳስባል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ እስር ላይ የሚገኙት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ እና ላዛሪስት ሚሲዮን ት/ቤት አካባቢ በሚገኘው ጉሌሌ ፖሊስ መምሪያ ታስረው የሚገኙት አቶ ካሳሁን ደስታ እስር ህገ ወጥ በመሆኑ የገዥው ፓርቲ እንዲፈታቸው ባልደራስ አበክሮ ያሳስባል፡፡
 
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
አዲስ አበባ
ታህሳስ 05/2015
የባልደራስ ፓርቲው አቶ ካሳሁን ደስታ በፖሊስ ታገቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ

Related Posts

ጋዜጣዊ መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል በፅንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኞች ፕሮግራማዊ ተልእኮ እየተመራ ያለው የአማራን ዘር የማጥፋት ኢ-ሰብዓዊና አፀያፊ ድርጊት ሊቆም ይገባል

ጋዜጣዊ መግለጫ

የደራ አማራን የዘር ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ጋዜጣዊ መግለጫ

የሰላም ድርድሩን አስመልክቶ ከባልደራስ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ።

Recent Posts

  • ሁለቱም የግፍ እስረኞች ለ ታህሳስ 19 ተቀጠሩ December 26, 2022
ባልደራስ Balderas logo
  • ዋና ገጽ
  • ዜና
  • ጋዜጣዊ መግለጫ
  • ፖ/ፕሮግራም
  • ምርጫ 2013
  • ባልደራስ ጋዜጣ
  • አባል ይሁኑ

ድል ለዲሞክራሲ!!!

© ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ Balderas for true democracy 2021