ዜና(News)
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከተገደሉት ንፁሃን መካከል የሰባቱ ሰዎች አስከሬን ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ
የኦሮሚያ ክልል ልዩ ኃይሎች የምስራቅ ወለጋ አጎራባች በሆነው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሚዢጋ ወረዳ ታንካራ ቀበሌ ታህሳስ 01/2015 ዓ/ም ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ የኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን የሰባቱን ሟቾች አስከሬን ብቻ መቅበር ተችሏል፡፡ በሀይል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የገቡት የኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የተገደሉ ህፃናት፣ሴቶችና አዛውንቶች አስከሬን በየጫካው ወድቆ More/ተጨማሪ…
የባልደራስ ፓርቲው አቶ ካሳሁን ደስታ በፖሊስ ታገቱ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ንቁ አባል እና ጉዳይ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ካሳሁን ደስታ ዛሬ ጠዋት፤ በትላንትናው ዕለት 03/04/2015 ዓ.ም ለታሰሩት አቶ ናትናኤል ስንቅ ለማቀበል ሄደው ነበር። ሆኖም በሄዱበት ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ (ላዛሪስት ፔኒሲዮን) የሚገኘው የጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በዛው አግቶ አስቀርቷቸዋል።አቶ ካሳሁን ፓርቲያቸውን እና ሀገራቸውን በትጋት እያገለገሉ የሚገኙ ሰላማዊ-ታጋይ ናቸው።
አቶ ናትናኤል የአለምዘውድ ታሰሩ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ንቁ አባል የነበሩት አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ባልታወቁ ደህንነቶች ዛሬ በሰፈራቸው ቀጨኔ መድሃኒአለም አካባቢ ተይዘዋል።አቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ቀድሞው ህወሃት መራሹ መንግስትም ሆነ በአሁኑ የኦሮሞ-ብልፅግና መራሹ መንግስት በተደጋጋሚ ታስረዋል።
በወቅታዊ የፓርቲያችን እንዲሁም የሀገራችን ሁኔታ ላይ የተደረገ ውይይት
የባልደራስ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት ዶ/ር በቃሉ አጥናፉና አቶ ስንታየሁ ቸኮል በወቅታዊ የፓርቲያችን እንዲሁም የሀገራችን ሁኔታ ላይ ተወያይተወዋል። ውይይቱን ከታች ባለው ሊንክ (Link) በመግባት ይከታተሉ።ሊንኩን ለመክፈት እዚህ ይጫኑ