ዜና(News)
በፕላዝማ መበላሸት ምክንያት በዛሬው ችሎት ሊዳኝ የነበረው የእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ለሚያዝያ 15 ተዛወረ !!
በጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚደረገው ችሎት ለዛሬ ሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ተቀጥሮ የነበረው ችሎት ‘ፕላዝማው ተበላሽቷል’ በሚል ለፊታችን ሚያዝያ 15 ቀን ተዘዋውሯል። ይኸው ችሎት ከዚህ በፊት ለመጋቢት 28 ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን ከሦስቱ ዳኞች መካከል አንዱ ባለመገኘታቸው ነበር ለዛሬ የተሸጋገረው።የህሊና እስረኞች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ከፕላዝማ ይልቅ በችሎቱ ፊት ለፊት ለመቅረብ More/ተጨማሪ…
“ጣምራ ፌደራሊዝም”
ኢትዮጵያ ብዙህ ስትሆን ብዙሃነትን ማስተናገድ ግዴታዋ ነው፡፡ ብዙሃነት ለማስተናገድ የሚያስችል ስርዓተ መንግሥት ስናስብ የፌደራል ሥርዓቱ ቀዳሚ አጀንዳ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የፌደራል ሥርዓቱን ህጸጾችና በጎ ጎኖች በመገምገም የፌደራል ሥርዓታችን ኢትዮጵያዊ እንዲሆን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚነሳው ኣንዱ ዋና ኣጀንዳ ይሄ ሲሆን አዲስ የፌደራል ሥርዓትን ለኢትዮጵያ ያስተዋውቃል፡፡ የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራል ሥርዓት ይባላል፡፡ የፌደራል ሥርዓት ጽንፈኛ የሆነውን ፖለካችንን More/ተጨማሪ…
በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግፉአንን ድምጽ ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ ነው
በዓለም ዙሪያ በተለይም በአሜሪካና በአውሮጳ ክፍለ ዓለማት የሚኖሩ እውነተኛ ሀገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጆች በዐማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች ለሆኑት የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች እስክንድር ነጋ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ የግፍ እስር የተቃውሞ ድምፃቸውን ማሰማት ቀጥለዋል። WASHINGTON, DC More/ተጨማሪ…
የባልደራስ እጩ አባላት በወቅታዊ የምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አደረጉ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባ ለፌዴራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለአዲስ አበባ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወከሉ እጩዎች በዛሬው እለት በራስ አምባ ሆቴል ፤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ የተለያዩ መርኃግብር እየተካሄደ ይገኛል ። የባልደራስ እጩ አባላት በወቅታዊ የምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አደረጉየዕለቱ መርኃግብር በግፉ ለተገደለው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ፓርቲ አባል ዕጩ More/ተጨማሪ…