ዜና(News)
ባልደራስ አጣዮን መልሶ ለመገንባት የሚውል ድጋፍ አደረገ !
ባልደራስ ለዕውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አጣየ ከተማን መልሶ ለመገንባት የተያዘውን መርሃ ግብር የሚያግዝ የግንባታ ቁሳቁስ ድጋፍ አደርጓል።ፓርቲው ለምርጫ ቅስቀሳ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የባነር መስቀያ ብረቶች እና እንጨቶችን መልሶ በመሰብሰብ ነው ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደረገው።ድጋፉን ለመስጠት በአጣየ ከተማ የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ሃላፊ የሆኑትን ወ/ሪት ዘቢባ ኢብራሂምን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው አባላት ተገኝተዋል።ባልደራስ ከዚህ ቀደም ከፖለቲካ ስራው ጎን ለጎን የተለያዮ More/ተጨማሪ…
ባልደራስ የምርጫ ቅስቀሳ የመዝጊያ መርሃ ግብሩን በደማቅ ሁኔታ አካሄደ !
ከፓርቲው ዋና ፅ/ቤት ጀምሮ በህዝባዊ እና በተሽከርካሪ ትዕይንቶች ታጅቦ በተለያዮ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የምረጡኝ የመዝጊያ ቅስቀሳውን አካሂዷል።በመርሃ ግብሩ ላይ የባልደራስ እና የአብን ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ፣ የፓርቲው የህዝብ እንደራሴ እና የክልል ም/ቤት ዕጩዎች፣የፓርቲዎች ደጋፊና አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪዎች ተገኝቷል።ፓርቲው ባካሂደው የመዝጊያ መርሃ ግብር ከተሳታፊዎቹ ባሻገር ከአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የነበረው አቀባባል ዕጅግ ከፍተኛ More/ተጨማሪ…
በአፍራሾቿ ዶማ ላይ የተኛችው አዲስ አበባ (ጌጥዬ ያለው)
አንድ ተረት አለ፤ ትዝ የሚለኝ፡፡ ሁለት ወንዶች በአውድማ ተኝተው ነው፡፡ በውድቅት ሌሊት ጅብ መጣና የአንደኛውን እግር እንደሸንኮራ አገዳ ሞሽልቆ መቆርጠም ጀመረ፡፡ ጓደኛው ድምፅ ሰምቶ ምን እየሆነ እንደሆነ ይጠይቀዋል፡፡ ፈሪው ጓድ ‹‹ጅብ ነው፡፡ ተወው እግሬን ብቻ ነው የሚበላው›› አለው ነው ተረቱ፡፡ ‹‹ታዲያ እግርህን ከበላው ነፍስህንም እንዳይበላት ይሆን የምትጨነቀው?›› በማለት ጅቡን አባረረው፡፡ ፈሪውም አንካሳ ሆኖ ቀረ፡፡ በሰሞኑ More/ተጨማሪ…
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ ፀረ-ሽብር ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ዛሬ ብይን ሰጥቷል
በ6ኛው አገራዊ ምርጫ እጩ ሆነው በመቅረባቸው ምክንያት ያለመከሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ አረጋግጦ ከእስር እንዲፈቱ በጠበቆች የቀረበው አቤቱታ ላይ ፍ/ቤቱ፣ የወንጀል ክሱ የተመሠረተው እጩ ሆነው ከመመዝገባቸው በፊት ስለሆነ ጥያቄውን አልተቀበልኩትም በማለት በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ ብይን ሰጥቷል።ጠበቆቹ በብይኑ ላይ ቅሬታ ስላደረብን ይግባኝ ለጠቅላይ ፍ/ቤት በማዘጋጀት ላይ እንገኛለን በማለት የህግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ More/ተጨማሪ…